Call for Accountability and Justice
(For immediate release)
(For immediate release)
For Immediate Release
We urge the TPLF and OLF to be unconditionally classified as terrorists now!
We would first like to express our deepest condolences to the mothers and fathers, brothers and sisters including children whose lives were sacrificed for just being an Amhara.
ትህነግ እና ኦነግ አሁንኑ በሽብርተኝነት እንዲፈረጁ አጥብቀን እንጠይቃለን!!!
የኢትዮጵያ መንግስት በአገሪቱ ያለዉን አለመረጋጋት ለመቆጣጠር ያስችለኛል ያለዉን የጥላቻ ህግ ረቂቅ አዋጅ ይፋ በማድረግ ህጉን በማፅደቅ ተግባራዊ ለማድረግ በእንቅስቃሴ ላይ ይገኛል። አገሪቱ ዉስጥ ያለዉ የፖለቲካ አለመረጋጋት መፍትሄ የሚሻ ጉዳይ መሆኑ አከራካሪ አይደለም። ዶ/ር አብይ ወደ ስልጣን ከመጡበት መጋቢት 24 2010 ዓ.ም ጊዜ ጀምሮ አግሪቱ በከፍተኛ የፖለቲካ ለዉጥና ነዉጥ ዉስጥ ትገኛለች። ለዉጡን ተከትሎ የመጣዉ የፖለቲካ ምህዳሩ መከፈት ግለሰቦች፥ የብሄር ድርጅቶችና ሚድያዎች ሃሳባቸዉን በአንፃራዊ ነፃነት የሚገልፁበት ሁኔታ ተፈጥሮ ነበር። የአገሪቱ የፖለቲካ አወቃቀር ብሄርን መሰረት ያደረገ በመሆኑ የፖለቲካ ምህዳሩ መከፈት ተከትሎ ብሄር ተኮር የፖለቲካ ሃይሎች በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች ተጠናክረዉ በመዉጣታቸዉ የብሄር ግጭት፥ መፈናቀል፥ ዝርፊያና አለመረጋጋት በተለያዩ አካባቢዎች ተከስቷል።[1] በቅርቡ በአማራና በደቡብ ክልሎች የተከሰቱትን ግጭቶች ተከትሎ መንግስት የሃይል እርምጃ በመዉሰድ
ጤና ለሰው ልጅ የተሰጠ ትልቁ ሃብት ነው። ሁሉ ነገር ተሟልቶ ጤንነት ከታወከ ተንቀሳቅሶ፡ ሰርቶና፡ ቤተሰብን መርቶ በደስታ መኖር አይቻልም። የጤንነት መታወክ የምክንያቱ ደረጃ ይለያይ እንጅ በየትም አገር የሚኖር የማንኛውም ማህበረሰብ እውነታ ነው። ስለሆነም አገሮች ሁሉ የዜጎቻቸውን ጤንነት ለመንከባከብ የጤና ተቋማትን አቋቁመውና ባለሙያዎችን አሰልጥነው የጤና ግልጋሎትን ይሰጣሉ። ከነዚህ የጤና ግልጋሎቶች አንዱ ክትባት ነው። በኢትዮጵያ የጤና እንክብካቤ አገልግሎት በጠቅላላው ብዙ የሚቀረው ቢሆንም በተለይ ‘አማራ ክልል’ በሚባለው ግን እጂጉን የባሰ ነው። ለዚህም ምክንያቱ ህወሓት ዐማራን ለማዳከም የተከተለው ሁለገብ የጠላትነትና የጥቃት ዘመቻ ነው። የዐማራ ሕዝብ ለክፋት መሳሪያነት ይሆናሉ ብሎ ባልገመታቸው የጤና ዐገልግሎትም በኩል ጭምር ወያኔ ከፍተኛ በደል ስላደረሰበት በጤና ተቋማትና በባለሙያዎች የሚሰጡ እንደ ክትባት የመሳሰሉ እጅግ አስፈላጊ የሆኑ የጤና እንክብካቤዎችን በጥርጣሬ እንዲመለከትም የተገደደበት ሁኔታ ተፈጥሯል። ሆኖም
ይህ የአማራን “ክልል” የጤና ሁኔታ ለመዳሰስ የተካሄደ አነስተኛ ጥናት የ “ክልሉን” የጤና ሁኔታ በሙሉ ለማሳየት ፍጹም በቂ ነው ባይባልም፣ አሁን አገራችን እያካሄደች ካለችው ለውጥና የ “ክልሉ” መንግስትም የህዝቡን ችግሮችና ጥያቄዎች ለመመለስ ካሳየው ተነሳሽነት አንጻር ያሉትን ጉልህ ችግሮች በማሳየት የውይይት መድረክ ለመክፈትና ሁሉም የበኩሉን አስተዋጾ እንዲያደረግ ለመጠቆም መነሻ እንዲሆን የቀረበ ነው። በዚህ ዳሰሳ ውስጥ የተመለከቱት ጉድለቶች ለአማራ “ክልል” ህዝብ በልማት ወደኋላ መቅረት ምክንያቱ አጠቃላይ የስርአቱ አድሉዊነት እደሆነ ጥሩ ማሳያዎች ናቸው። “ክልሉን” የሚያስተዳድርው ብአዴንም(አሁን አዴፓ ተብሏል) ለአማራ ጥቅም ከመቆም ይልቅ ለትህነግ ተልኮ አስፈጻሚነት ቆሞ እንደቆየ በስፋት የተባለውን ማሳያ ነው።
የአዮዲን እጥረት ችግር ምንድን ነው? አዮዲን በተፈጥሮ በውሃና በአፈር ውስጥ የሚገኝ ንጥረ ነገር ነው። አዮዲን በባሕር ውስጥ በብዛት የሚገኝ ንጥረ ነገር ሲሆን በመሬት እና በንጹህ ውሃ ላይ ያለው ስርጭት ግን ከቦታ ቦታ ይለያያል። በጊዜ ብዛት በአፈር ውስጥ ያሉት የተፈጥሮ ንጥረ ነገሮች መመናመን የአዮዲንንም መጠን በከፍተኛ ደረጃ የቀነሰው በመሆኑ በርካታ የኢትዮጵያ መሬት በተለይም ተራራማው የሆነው የዐማራ መኖሪያ ቦታዎች የተፈጥሮ አዮዲኑ ተመናምኗል። ስለዚህም በአለም በሙሉ እንደሚደረገው ለህዝብ በሚቀርበው ጨው ላይ አዮዲን መጨመር የተለመደ ነው። በቂ አዮዲን ያላገኙ ሰዎች የታይሮይድ ሆርሞን እጥረት (hypothyroidism) ያጋጥማቸዋል ውጤቱም የታይሮይድ ዕጢ እብጠት (እንቅርት) ይሆናል። ይህም በህጻናት ላይ ሲደርስ እድገትን ያቀጭጫል፤ የአእምሮ እድገትን በከፍተኛ ደረጃ ይጎዳል።
አምንስቲ ኢንተርናሽናል ባወጣው ሪፖርት ኢትዮጵያ ውስጥ በአሁኑ የአስተዳደር አከላለል "ኦሮምያ" ተብሎ በሚጠራው አካባቢ አማራዎች እየደረሰባቸው ያለውን ግድያ እና መፈናቀል አትቶል:: በቀጣይ ከዚህ ጠንከር ያለ እና ዝርዝር ማጣራት እንደሚያደርግ እና ጉዳዪን ሪፖርት እንደሚያደርግም አሳውቆል::
Ethiopia: Government must protect victims of escalating ethnic attacks
The Ethiopian government must intervene to protect thousands of ethnic Amharas who are on the verge of displacement due to violent attacks on their homes by ethnically-motivated youth groups in Oromia Regional State, Amnesty International said.
ውድ የአምባ ተከታዮች፣
አምባ የአማራ ባለሞያዎች ማህበር በሞትና ህይዎት መሃል ያለውን የ14 ዓመት ታዳጊ አበጠር ወርቁትን ለመታደግና እና በአገራቸው "መጤ" ተብለው የተፈናቀሉ የአማራ ተወላጆችን ለመርዳት የgofundme ዘመቻ ጀምሯል።
እባክዎን የቻሉትን ያህል አስተዋጽዖ ያድርጉ።
Dear followers of Amba,
Amba has launched a GoFundMe campaign to save Abetir Worku and help the displaced Amhara.
Please contribute what you can, nothing is too small for the people who lost everything!
https://www.gofundme.com/save-abetir-w-help-displaced-amara?member=200192