የአዮዲን እጥረት ችግር ምንድን ነው? አዮዲን በተፈጥሮ በውሃና በአፈር ውስጥ የሚገኝ ንጥረ ነገር ነው። አዮዲን በባሕር ውስጥ በብዛት የሚገኝ ንጥረ ነገር ሲሆን በመሬት እና በንጹህ ውሃ ላይ ያለው ስርጭት ግን ከቦታ ቦታ ይለያያል። በጊዜ ብዛት በአፈር ውስጥ ያሉት የተፈጥሮ ንጥረ ነገሮች መመናመን የአዮዲንንም መጠን በከፍተኛ ደረጃ የቀነሰው በመሆኑ በርካታ የኢትዮጵያ መሬት በተለይም ተራራማው የሆነው የዐማራ መኖሪያ ቦታዎች የተፈጥሮ አዮዲኑ ተመናምኗል። ስለዚህም በአለም በሙሉ እንደሚደረገው ለህዝብ በሚቀርበው ጨው ላይ አዮዲን መጨመር የተለመደ ነው። በቂ አዮዲን ያላገኙ ሰዎች የታይሮይድ ሆርሞን እጥረት (hypothyroidism) ያጋጥማቸዋል ውጤቱም የታይሮይድ ዕጢ እብጠት (እንቅርት) ይሆናል። ይህም በህጻናት ላይ ሲደርስ እድገትን ያቀጭጫል፤ የአእምሮ እድገትን በከፍተኛ ደረጃ ይጎዳል።
Is Amharic?
More To Read