ዐማራው ላለፉት 50 ዓመታት ዐማራነቱ የጥቃት ኢላማ አድርጎት ቆይቷል። ላለፉት 30 ዓመታት ደግሞ ሕግ ወጥቶለት በሕገ መንግስት ተጠቅሶ ጸረ ዐማራነት የሀገሩ ሕግ ሆኗል። ይህ ሲሆን ታዲያ ዐማራው በራሱ ላይ የታወጀውን ፀረ ዐማራነትና ፀረ ዐማራ ሕግ በሚገባ ተረድቶ ሲታገለው ቆይቷል ለማለት አይቻልም። “ሕገ መንግስት” ተብዮውን ሲተች የቆየው “በዘር የተካለለ አስተዳደር ለኢትዮጵያ አይጠቅምም” ወይንም ኢትዮጵያን እንደ ሀገር አያይም በማለት እንጂ ዋና ማጠንጠኛ ሐሳቡና የአስተዳደር አከላለሉ ዐማራን ለመጉዳትና ለማግለል እንዲሁም አገር አልባ ለማድረግ ነው በሚል አልነበረም።
የአብይ አህመድ አገዛዝ ላለፉት ስድስት ዓመታት መንበሩን በኢትዮጵያ ላይ ከጫነ በኋላ ደግሞ ዐማራውን በአደባባይ እንዲፈናቀል፣ እንዲገደል፤ እንዲጨፈጨፍ፣ በዶዘር እየተማሰ እንዲቀበር ተደርጓል እየተደረገም ነው። ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ፤ በቆረቆራት አዲስ አበባ ለጉዳይም ይሁን ለህክምና መውጣትና እና መግባት ቅንጦት ከሆነ ቆይቷል። በግልጽ በአገዛዙ የታጠቀ ኃይል ተደብድቦ ይመለሳል ወይም አገዛዙ ባደራጃቸው ሽፍቶች ታፍኖ ገንዘብ ይደራደሩበታል።
Is Amharic?
More To Read