የጥላቻ ንግግር ህግ አዋጅና እድምታዎቹ

መግቢያ

የኢትዮጵያ መንግስት በአገሪቱ ያለዉን  አለመረጋጋት ለመቆጣጠር ያስችለኛል ያለዉን የጥላቻ ህግ ረቂቅ አዋጅ ይፋ በማድረግ ህጉን በማፅደቅ ተግባራዊ ለማድረግ በእንቅስቃሴ ላይ ይገኛል።  አገሪቱ ዉስጥ ያለዉ የፖለቲካ አለመረጋጋት መፍትሄ የሚሻ ጉዳይ መሆኑ አከራካሪ አይደለም። ዶ/ር አብይ ወደ ስልጣን ከመጡበት መጋቢት 24 2010 ዓ.ም ጊዜ ጀምሮ አግሪቱ በከፍተኛ የፖለቲካ ለዉጥና ነዉጥ ዉስጥ ትገኛለች። ለዉጡን ተከትሎ የመጣዉ የፖለቲካ ምህዳሩ መከፈት ግለሰቦች፥ የብሄር ድርጅቶችና ሚድያዎች ሃሳባቸዉን በአንፃራዊ ነፃነት የሚገልፁበት ሁኔታ ተፈጥሮ ነበር። የአገሪቱ የፖለቲካ አወቃቀር ብሄርን መሰረት ያደረገ በመሆኑ የፖለቲካ ምህዳሩ መከፈት ተከትሎ ብሄር ተኮር የፖለቲካ ሃይሎች በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች ተጠናክረዉ በመዉጣታቸዉ የብሄር ግጭት፥ መፈናቀል፥ ዝርፊያና አለመረጋጋት በተለያዩ አካባቢዎች ተከስቷል።[1] በቅርቡ በአማራና  በደቡብ ክልሎች የተከሰቱትን ግጭቶች ተከትሎ መንግስት የሃይል እርምጃ በመዉሰድ ብዙዎች ለእስር ተዳርገዋል። [2] መንግስት ከፍተኛ ተቃዉሞ የቀረበበትን የ ፀረ ሽብርተኝነት ህጉን በመጠቀም የሰብአዊ መብት ተከራካሪዎች ላይ ክስ ማቅረቡ ለዉጡ እየተቀለበሰ ነዉ የሚል ስጋት አድሮባቸዋል። አገሪቱ ዉስጥ ካለዉ ዘርን መሰረት ባደረገዉ የፖለቲካ ስርአት ምክንያት የዘር መከፋፈልና ጥላቻ እየተስፋፋ በመምጣቱ የጥላቻ ህግን ማዉጣት በመርህ ደርጃ አስፈላጊ ቢሆንም የህጉ መዉጣት የሚያስከትለዉን ችግር ማንሳት አስፈላጊ ነዉ። ይህ ፅሁፍ የጥላቻ ህግ ታሪካዊ አመጣጥ ፥ አለም አቀፍ ልምዶችና በኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ ባለዉን ህገ መንግስታዊ ስርአትና ፖለቲካዊ ሁኔታ አንፃር በመዳሰስ የመፍትሄ ሃሳቦችን ለመጠቆም ይሞክራል።

 

[1] Ethiopia: 3 million internally displaced in escalating humanitarian crisis, https://www.euronews.com/2019/01/31/ethiopia-3-million-internally-displaced-in-escalating-humanitarian-crisis

[2] In era of reform, Ethiopia still reverts to old tactics to censor press, https://cpj.org/blog/2019/07/ethiopia-coup-internet-censored-blocked-jailed-journalists.php

 

ለቀጣዩ የሚከተለውን pdf ይጫኑ

Is Amharic?
More To Read