እንቆቅልሽ

እንቆቅልሽ

በአለም አቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ እዉቅና ያተረፉትን እስረኞች ብቻ ለቆ በተመሳሳይ ክስ ምንም በማያዉቁት የታሰሩትን ወንድሞቻችንን ወደ ከፋ የጨለማ ቤት አዉርዶ ማሰቃየት ምን ይባላል? በዶ/ር አብይ የሚመራዉ የኢትዮጵያ መንግስት እስረኞችን ከጎረቤት ሀገር ድረስ ተደራድሮ ማስመለሱ የሚታወስ ሲሆን፦ ወንድሞቻችን በጨለማ ሲሰቃዩ እየሰማ እያየ ለምን ዝም አለ? ለዉጡ የአለም አቀፉን ማህበረሰብ ማማለል ወይስ እዉነተኛ ለሀገርና ለህዝብ የታሰበ ለዉጥ ነዉ? የአማራ ህዝብ አሁንም ብዙ ያልተመለሱ ጥያቄዎች አሉት። ህዝቡ ጥያቄዎቹ ሳይመለሱ ይህ ሁሉ ስቃይ አሁንም እየደረሰበትና እየተመለከተ ከኖረበት ቀየዉ እየተሰደደና አሁንም እየተገደለ በምን መስፈርት ነዉ በደፈናዉ በጭፍኑ የመጣዉን ለዉጥ ሆ ግር ብለህ ተከተል ሊባል የሚችለዉ? እንቆቅልሽ ነዉ እንቆቅልሽ!

ከአማራ ድርጅቶች እና ማህበራት ስብስብ(አድማስ) የተሰጠ መግለጫ

 

መጋቢት 18, 2010  
 
በትግሬ ሕዝብ ነፃ አውጭ ግንባር(ትሕነግ) የሚመራው ዘረኛና ከፋፋይ፣ ፀረ-ኢትዮጵያና ፀረ-ዐማራ የሆነው  ድርጅት የሚመራው ኢሕአዴግ ፣በ27 ዓመታት አረመኔአዊ አገዛዝ በአገሪቱ ብሔራዊ ጥቅም፣ ግዛታዊ አንድነት፣ በሕዝቡ አብሮነት ስሜት ላይ የፈጸማቸው አፍርሽ ተግባሮች ኢትዮጵያን እንደ አገር ልትቀጥል ወደ ማትችልበት አደገኛ አዘቅት ውስጥ እየከተታት እንዳለ ይታወቃል። ከዚህ አስከፊ የመበታተን እና የእርስ በርስ እልቂት መውጣት እንዲቻል፣ ዜጎች በዜግነታቸው፣ የፖለቲካ፣ የሲቪክ፣ የሙያ ማኅበራትና የብዙኃን መገናኛዎች አገሪቱና ሕዝቡ ከአስከፊ ጥፋት ራሳቸውን መከላከል እንዲችሉ በየፊናቸው የተቻላቸውን ሲያስተምሩና ሲመክሩ የነበሩና ያሉ ግለሰቦችን ከመግደልና ከማሰደድ የተረፉትን በሀሰት ክስ ወንጅሎ ለበርካታ ዓመታት አስሮ ማሰቃየቱ ይታወቃል።  

ሰላም ቀለብ አይፈጅም

ከሁሉ አስቀድሞ እግዚአብሔር ከእስር ያስፈታቸዉን ውድ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን እንኳን ደስ አላችሁ እያልን፤ በአሁኑ ሰዓትም ማህበራዊ ሚድያ ያላወቃቸው እጅግ በጣም ብዙ የሚሆኑ ሽማግሌዎ፣ ወጣቶች፣ የፓለቲካ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዋች፣ ጋዜጠኞችና የሀይማኖት አባቶች በፌደራል እና በክልል እስር ቤቶች እንደሚገኙ በቅርብ ከተፈቱት ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ምስክርነት ለመረዳት ችለናል።

Press Release for the Upcoming Weyane Instigated "Kimant Referendum"

ቅማንትን እና ዐማራን ለመለያየት የሚደረገውን ሴራ  በመቃወም የዐማራ ድርጅቶች እና ማህበራት ያወጡት የጋራ  መግለጫ!

የትግራይ ሕዝብ ነፃ አውጭ ግምባር(ትህነግ)  ቁንጮ  በመለስ ዜናዊ ፥  በአባይ ፀሐዬና በስብሃት  ነጋ በ1968  ተረቆ በትህነግ   ማኒፌስቶ  በጉልህ ተቀምጦ የኖረውና  ትህነግ    ሥልጣን ከጨበጠም  በሗላ ያልተወው  መሪ ሃሳብ “ዐማራ የትግራይ ህዝብ ታሪካዊ ጠላት ነው”  የሚል ሲሆን ይህንን መርህ ተከትሎ ይህ ፋሽስታዊ  ድርጅት  የዐማራን ሕዝብ ሲገድል ፥ ሲያፈናቅል ፥  ለብሽታ ለረሃብና ለእርዛት ሲዳርግ ፥  እንዲሁም   ወላድ አንስቶቻችንን በመድሃኒት ሲያመክን እነሆ  አራት አሥርት አመታት ተቆጥረዋል::

አዲስ አበባ በረራ ናት፤ በረራም አዲስ አበባ

      በሀቅ ላይ የተመሰረተ ታሪክ ጽኑ የአንድነት መሰረት ነው። ፍትህንም ለማስፈን ወሳኝ ሚና አለው። ታሪክ የራሱ የሆነ የሙያ ስነምግባር ለውየታሪክ ባለሙያ ለሙያው ፍቅርም ሲል ህይወቱን መስዋዕት ለማድረግ ዝግጁ መሆን አለበት። የሚያስከፋም ሆነ የሚያስደስት፣ የሚያስነቅፍም ሆነ የሚያስወድስ በመረጃ የተመሰረተ ሀቀኛ ታሪክን መቀበል የስልጡንነት ምልክት ነው። ታሪክን መፍራት፣ መካድ እና ማድበስበስ ኋላቀርነት ነው። ታማኝ መረጃ እስከተገኘ ድረስ ታሪክ ያለምንም ገደብ ይጻፋል። ያስከፋል ወይም ያስነቅፋል ብሎ በታሪክ ላይ ሀጢያት መስራት ጉዳቱ ከባድ ነው። የታሪክ ዕውቀት ያድጋል፣ ይሰፋል ይቀየራል። ይህ የሚሆነው ደግሞ አዳዲስ መረጃዎች በአይነትና በመጠን ሲገኙ ነው።

Amara Advocacy in the US

As you know, Amba/APU is currently fighting very hard for the passage of HR 128 and SR 168.  For those of you, who want to know the exact wording of these resolutions, the links are presented below.


  1. House Resolution 128: Supporting respect for human rights and encouraging inclusive governance in Ethiopia (HR 128)
     

    Specifically, this resolution addresses the atrocities committed against us Amharas in two places: