የዐማራ ሕዝብ የህልውና ትግል ሂደትና ትግሉን ለመጥለፍ በፋኖ አመራሮች ላይ የሚደረግን ጣልቃ ገብነት በሚመለከት ከዐምባ የተሰጠ መግለጫ
ዐማራው ላለፉት 50 ዓመታት ዐማራነቱ የጥቃት ኢላማ አድርጎት ቆይቷል። ላለፉት 30 ዓመታት ደግሞ ሕግ ወጥቶለት በሕገ መንግስት ተጠቅሶ ጸረ ዐማራነት የሀገሩ ሕግ ሆኗል። ይህ ሲሆን ታዲያ ዐማራው በራሱ ላይ የታወጀውን ፀረ ዐማራነትና ፀረ ዐማራ ሕግ በሚገባ ተረድቶ ሲታገለው ቆይቷል ለማለት አይቻልም። “ሕገ መንግስት” ተብዮውን ሲተች የቆየው “በዘር የተካለለ አስተዳደር ለኢትዮጵያ አይጠቅምም” ወይንም ኢትዮጵያን እንደ ሀገር አያይም በማለት እንጂ ዋና ማጠንጠኛ ሐሳቡና የአስተዳደር አከላለሉ ዐማራን ለመጉዳትና ለማግለል እንዲሁም አገር አልባ ለማድረግ ነው በሚል አልነበረም።