የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት መግቢያ የምስክር ወረቀት ፈተና
አምባ (የአማራ ምሁራንና ባለሙያዎች) ማሕበር የ12ኛ ክፍልን ወደ ከፍተኛ ትምሕርት መግቢያ ፈተናን በተመለከተ የተከሰቱትን ኹኒታወች በትኩረት እየተከታተልን ሲሆን፥ የተፈጠረውም ነገር በጣም አሳስበውናል።
በትሕነግ ወረራ እና በተራዘመው ጦርነት የተከሰተው ውድመት፥ መፈናቀል እና አልመረጋጋት፤ በአብዛኛው ሕዝባችን በተለይም በወጣት ተማሪዎች ትልቅ ማኅበራዊ ቀውስ ይፈጠረና እየፈጠረ ያለ ክስተት ነው። በተጨማሪም ባለፈው ዓመት ሁን ተብሎ ማለፍ የሚገባቸው ተማሪወች እንዲወድቁ ስለተደረገ። ይህም በመማር ማስተማር ሒደቱ ከፍተኛ አሉታዊ ተጽዕኖ በመፍጠሩ፥ ድርጅታችን ላለፉት ሶስት ወራት እንደ አማራ ተማሪዎች ማህበር ፥ የክልሉ መምህራን የአማራ የአደጋጊዜ ስብስብ ከወንፈል ተራድኦና እንድሁም ከተለያዩ ግለሰቦች ጋር በመሆን ተማሪዎችን ለፈተና እንዲዘጋጁ ሲረዳ መቆየቱ ይታወሳል።
በፈተናው ወቅት የተረጋጋ እና ሰላም የሰፈነበት ከማንኛውም ሁከት የጸዳ ሁኔታ መፍጠር።ሊከሰቱ የሚችሉአንዳንድ እክሎችን እንደአመጣጣቸው መፍታት ከመንግሥት የሚጠበቅ ኃላፊነት ሲሆን የጸጥታ አስከባሪዎችም አካባቢውን የጦር ቀጠና ከሚያስመስል ሁከት ማስነሳት መቆጠብ ይገባቸዋል። ይሕን ያሕል ለበርካታ ወራት ዝግጅት ያደረጉ በሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች በግብታዊነት ፈተናውን ረግጠው ወጡ የሚለው የጅምላ ፍርጃ አብዛኞችን ታታሪ እና ሥነ ሥርዓት እሚያከብሩ ተማሪዎች የሚያንቋሽሽ መላምት ነው።
በክስተቱ ላይ ሁሉንም ወገን ያካተተ ማጣራት እንዲደረግና ፍትህ እንዲሰጥ ፥ ይህ እስኪሆን ድረስም ፍረጃውእንዲቆም ጥሪ እናደርጊለን።
የኢፌዴሪ ት/ሚንቴርም በጅምላ መፈረጁን በመተው ሁሉንም ወገን ያካተተ አጣሪ ቡድን አቋቁሞ፥ በሁሉምዘንድ ተቀባይነት ያለው ፍትሕ እንዲ በይን እናሳስባለን። ውሳኔው ከሌላው የአገራችን ክፍል ያሉ ተማሪዎች በተለዬ የወራሪ ሰለባ በሆኑ፥ በጦርነትና መፈናቀል እና የሕልውና ዘመቻ ውስጥ ሆነው ዝግጅት ያደረጉ እንዲሁም በአምናው ተመሳሳይ ፈተና ላይ የተፈፀመው መንግስታዊ ሸፍጥን የሚዪስታውስ ፥ በብዙሺ ተስፈኛ ተማሪዎች እና ቤተሰቦቻቸው ላይ የሚፈጥረው ጫና በአካባቢው ሰላምና እና መረጋጋት ላይ ቀጥተኛ ተጽዕኖአለው።
የምሁራን ማሕበር እንደመሆኑ መጠን አምባ ለትምሕርት አትኩርት ስጥቶ እና ጠንክሮ መሥራትን ያበረታታል ፥ የላቀ ሙያዊ ስነምግባር ለሕረተሰብ አቀፍ ለውጥ አስፈላጊ ነው ብሎ በአጽንዖት ያምናል። በመሆኑም ተፈታኞች የገጠማቸውን እክል፥ ከሚመለከታቸው የተማሪዎች ማ ሕበራት፥ የመምህራን ማሕበራት፥ቅሬታ ስሚ እና መፍትሄ አፈላላጊ አካላት፥ ህግ አስፈጻሚ ተቋማት ጋር ተድራጅተው መፍትሔመፈለግና እንደገና የሚፈተኑበት ሁኔታ እናዲፈጠርላቸው መጣር ያስፈልጋል።
የአማራ ተማሪዋችና የህብረሰባችን ችግር ዘርፈ ብዙ መሆኑንን ስንረዳ ተማሪዎችም የመፍትሄው አንድአካል መሆናቸውንም እንገነዘባለን ስለዚህም በሁሉም ወገን አዋንታዊ ተካፋይነት የተማሪዋቹን ና የቤተሰቦቻቸውን ችግር ተረድቶ በክልሉ ለረዘመ ጊዜ ከሚኪያሄደው ጦርነት መከራ አንፃር ግንዛቤም እንዲወሰድ እንጠይቃለን ::
አምባ
ስራ እስኪጂ ኮሚቴ